የአለማቀፍ የነዳጅ ፍጆታ ከኮሮና ወረርሽኝ በኋላ ጭማሪ አሳይቶ በ2024 እለታዊ የነዳጅ ፍጆታ 103 ሚሊየን በርሚል ደርሷል። በአፍሪካ በየእለቱ 3.5 ሚሊየን በርሚል ነዳጅ ጥቅም ላይ እንደሚውል የአለማቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ መረጃ ያሳያል። እንደ ናይጀሪያ፣ አንጎላ እና አልጀሪያ ያሉ ነዳጅ አምራች ሀገራት የሚገኙባት አፍሪካ የድፍድፍ ነዳጅ ፍጆታዋ እየጨመረ መምጣቱን ቢዝነስ ኢንሳይደር አስነብቧል። ለዚህም የግዙፍ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት፣ የከተሞች እድገት […]
National statistics
ከፍተኛ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
የተሸለ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገራት ለዜጎቻቸው ከሚያቀርቧቸው አገልግሎቶች ውስጥ ለሰራተኞቻቸው የሚያስቀምጡት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አንዱ ነው፡፡ በዚህም መሰረት አነስተኛ ህዝብ ብዛት ያላት ሉግዘምበርግ በአማካኝ 8 ሺህ ዶላር ወርሃዊ ደመወዝ በመክፈል ከዓለም ቀዳሚዋ ሀገር ናት፡፡ የአውሮፓ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ቤልጂየም 7 ሺህ 500 ዶላር አማካኝ ወርሃዊ ደመወዝ ስትከፍል ኔዘርላንድ ደግሞ 7ሺህ 500 ዶላር ትከፍላለች፡፡ ኖርዌይ፣ ኦስትሪያ እና […]
የዓለማችን ተወዳጅ 10 ስሞች የትኞቹ ናቸው?
ስም ከማህበራዊ ማንነት መገለጫዎች መካከል አንዱ ሲሆን ወላጆች ልጆቻቸውን ከማንነታቸው ጋር ተያያዥ የሆኑ እና ትርጉም የሚሰጡ ስሞችን ይሰጣሉ። ከወላጆች እና ህጻናት ጋር የተያያዙ መረጃዎችን በማውጣት የሚታወቀው ፓረንትስ ዶት ኮም የተሰኘው ድረገጽ እንዳስነበበው ከሆነ ሙሃመድ በአሁኑ ወቅት በብዛት ህጻናት የሚጠሩበት ቀዳሚው ስም ሆኗል፡፡
የ2025 ምርጥ 10 የዓለማችን ዩንቨርስቲዎች የትኞቹ ናቸው?
የደቡብ አፍሪካው ዊትዋተርስራንድ ዩንቨርሲቲ ከአፍሪካ ቀዳሚው ሆኗል የዓለማችን ዩንቨርሲቲዎችን በሚቀበሉት ተማሪዎች ብዛት፣ በሚያሳትሟቸው አዲስ ምርምሮች፣ በምሁራን ቁጥር እና ሌሎች መስፈርቶችን መነሻ በማድረግ የዩንቨርሲቲዎች ደረጃ ይወጣል፡፡ ታየምስ ኦፍ ሀይር ኢዱኬሽን የተሰኘው ተቋም የ2025 የዓለማችን ዩንቨርሲቲዎችን ደረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን የብሪታንያ እና አሜሪካ ዩንቨርሲቲዎች ከ1 እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ ተቆጣጥረዋል፡፡ ኦክስፎርድ ዩንቨርሲቲ ፣ ማሳቹሴትስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና […]
ለ2017 በጀት አመት 1ኛ አዲስአበባ ዩንቨርሲቲ 1.9 ቢሊዮን ብር፣ 2ኛ ባህርዳር 1.8 ቢሊዮን ብር ተመድቦላቸዋል
ከአንድ ሺህ በላይ ፕሮጀክቶች ለሚያስተዳድሩት ዩኒቨርሲቲዎች፤ የፌደራል መንግስት 39 ቢሊዮን ብር በጀት መደበ። ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ የተመደበላቸው የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 13 ናቸው።
የመጭው 2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 971.2 ቢሊየን ብር ሆኖ ለፓርላማው ቀረበ፡፡
ይህም ከ2016 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ የወጪ በጀት ውስጥ 451.3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ በጀት፣ 283 .2 ቢሊየን ለካፒታል እንዲሁም 236.7 ቢሊየን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍሆኖ መደልደሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ለክልሎች ከተመደበው በጀት ውስጥ 14 ቢሊየን ብር የሚሆነው የዘላቂ ልማቶችን ለማስፈፀም ለክልሎች የተመደበ […]
በኢትዮጵያ 2 ሚሊየን ዜጎች በየዓመቱ ስራ አጥ ይሆናሉ ተባለ
በኢትዮጵያ 71 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም የሚፈጠረው የስራ እድል ግን ከ50 በመቶ በታች መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ወንድማገኝ ታዬ ለአራዳ ገልጸዋል። በዚህም በየዓመቱ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ዜጋ ስራ አጥ እንደሚሆን የሴንትራል ስታቲስቲክስ ዳታ ጥናት ያመላክታል ነው ያሉት ባለሙያው። የህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር አለመመጣጠን፣ ከማምረቻው ዘርፍ ይልቅ የአገልግሎት […]
ከሬሚታንስ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ ሀገራት
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ሰዎች ወደ ሀገራቸው የሚልኩት የውጭ ምንዛሬ (ሬሚታንስ) በ2023 የ3 ነጥብ 8 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ባለፈው የፈረንጆቹ አመት በሬሚታንስ የተላከው ገንዘብ 669 ቢሊየን ዶላር መድረሱንም የአለም ባንክ መረጃ ያሳያል። ከሬሚታንስ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ ሀገራትን በዝርዝር ይመልከቱ
ኢንተርኔት በመዝጋት ከፍተኛ ገቢ ያጡ የዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
ሩሲያ 113 ሚሊዮን ዜጎቿን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ በማድረግ ቀዳሚዋ ሀገር ተብላለች ኢትዮጵያም ሌላኛዋ ኢንተርኔት ለረጅም ጊዜ የዘጋች ሀገር ስትሆን 1.6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገልጿል ምንጭ:- አልአይንተ










