የ2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች አጠቃላይ አሃዛዊ መረጃ
ከ896 ሺህ 520 ተማሪዎች ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ 29 ሺህ 909 (3.3 በመቶ) ናቸው
• የተፈተኑ ተማሪዎች ቁጥር 896 ሺህ 520
• በፈተናው ላይ ተመዝግበው ያልተገኙ ተማሪዎች 77 ሺህ 98
• በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች እንዳይፈተኑ የተደረጉ 20 ሺህ 170
• ከተፈጥሮ ሳይንስ የተፈተኑ 339 ሺህ 642 ሲሆኑ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 22 ሺህ 936 (6.8 በመቶ)
• ከማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ 586 ሺህ 878 ሲሆኑ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች 6 ሺህ 973 (1.3 በመቶ)
• በአጠቃላይ ከ896 ሺህ 520 ውስጥ ከ50 በመቶ በላይ ያመጡ ተማሪዎች ብዛት 29 ሺህ 909 (3.3 በመቶ)
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው ከ700፤ 666
• ከማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው ከ600፤ 524
• በፆታ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 666፤ ሴት 650
• በፆታ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት በማህበራዊ ሳይንስ ወንድ 516፤ ሴት 524
• በተፈጥሮ ሳይንስ 600 እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 263
• በማህበራዊ ሳይንስ 500 እና ከዛ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 10
• በአጠቃላይ መደበኛ ተማሪዎችን ያስፈተኑ ትምህርት ቤቶች 2ሺሕ 959
• ከዚህ ውስጥ ሁሉንም ተማሪዎቻቸውን ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ብዛት 7
• አዲስ አበባ፣ ድሬደዋ እና የሀረሪ ክልል የተሻለ ውጤት የተመዘገበባቸው አካባቢዎች ናቸው።





