Ethiopia | ግሎባል ፋይናንስ ለ30ኛ ጊዜ የ2023 የሀገሮች ምርጥ ባንኮችን ይፋ ያደረገ ሲሆን አዋሽ ባንክም ከኢትዮጵያ ለ2ኛ ጊዜ ምርጥ ባንክ ተብሎ መመረጡን አስታውቋል።
የሀብት እና ትርፍ መጠን እድገት፣ ተደራሽነት፣ ስትራቴጂክ ግንኙነት፣ አዳዲስ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ ባንኩ ተወዳድሮ ካሸነፈባቸው መስፈርቶች መካከል ናቸው ።
የባንኩ ሲኒየር ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር ዮሃንስ መርጋ፣ አዋሽ ባንክ በግሎባል ፋይናንስ መጽሔት ዳግም ምርጥ ተብሎ መመረጡ ባንኩ እየሄደበት ያለውን የእድገት ጉዞ ማሳያ ነው ብለዋል።
ባንኩ ዳግም ምርጥ ተብሎ መመረጡ የሀገሪቱን የፋይናንስ ዘርፍ ገጽታ ይበልጥ ለማሳደግ ያግዛል ያሉት አቶ ዮሀንስ ፣ ሽልማቱን በዓለም አቀፋ የገንዘብ ተቋም ወይም በአለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ በሞሮኮ ማራካሽ ይቀበላል ብለዋል።
ግሎባል ፋይናንስ በአፍሪካ አዋሽ ባንክን ጨምሮ 36 ባንኮች መርጧል።
በአባዲ ወይናይ



