Ethiopia | የእንግሊዝ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋቾች ማህበር የ 2023 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ይፋ አድርገዋል።
በዚህም መሰረት የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ የ 2023 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።
በተመሳሳይ፣ እንግሊዛዊው የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል የፊት መስመር ተጨዋች ቡካዩ ሳካ የ2023 የፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጨዋች በመሆን መመረጥ ችሏል።
በሌላ በኩል፣ የ2023 የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተጨዋቾች የዓመቱ ምርጥ ወጣት ሴት ተጨዋች የቼልሲዋ ላውራን ጀምስ በመሆን መመረጧን ቢቢሲ ዘግቧል።






