Ethiopian stat Home National statistics

ዘንድሮ በተሰጠው የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና /Exit Exam/ 40.65% ብቻ ሲያልፉ 59.35% ወድቀዋል

ፈተናውን ለመውሰድ ከተመዘገቡት ከመንግስት 77ሺ 981 ወይም 92 ነጥብ 15 በመቶ ከግል 72ሺ 203 ወይም 65 ነጥብ 87 በመቶ በድምሩ 150ሺ 184 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ተናግረዋል።

ከመንግስት ተቋማት ለፈተና ከተቀመጡት 48ሺ 632 ተማሪዎች ውስጥ 62 ነጥብ 37 በመቶ ከግል ተቋማት ተማሪዎች ውስጥ ደግሞ 17 ነጥብ 2 በመቶ የማለፊያውን 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል።

በድሞሩ ለመውጫ ፈተናው ከተቀመጡት 61ሺ 54 ተማሪዎች 40 ነጥብ 65 በመቶ የማለፊያውን ነጥብ ማስመዝገባቸውን ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸዋል።

በመውጫ ፈተናው የሚፈለገውን የማለፊያ ውጤት ያላስመዘገቡ ቅድመ ምሩቃን ተማሪዎች ፈተናውን በየሰድስት ወሩ ደጋግመው መውሰድ እንደሚችሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *