Home National statistics

ኢትዮጵያ ከፍተኛ ግጭት ካለባቸው አገራት አንዷ ሆነች

ዓለም አቀፍ የግጭት ክስተት መረጃዎችን በመተንተን የሚታወቀው “The Armed Conflict Location & Event Data Project” (ACLED) የተሰኘ መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋም፣ አዲስ ባወጣው የግጭት ኢንዴክስ ኢትዮጵያን ከፍተኛ ግጭት ካለባቸው አገሮች መካከል መድቧታል፡፡

አክሌድ ያወጣው የዓለም አገራት የግጭት ኢንዴክስ እንደሚያመላክተው ከሆነ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 25ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ኢትዮጵያ አሁን የምትገኝበት ከፍተኛ የግጭት ሁኔታ ወደ አደገኛ ደረጃ ሊሸጋገር የሚችለበት ደረጃ ከፍተኛ መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የአገራቱ የግጭት ሁኔታ ደረጃ የሚመዘነው በዋናነት የሰላማዊ ሰዎች ለግጭት ሰለባነት፣ የግጭቶች የመልዕክ ምድራዊ ስርጭት፣ በታጣቂ ኃይሎች ክፍፍና በግጭት የጊዜ ቆይታ መሰረት ነው፡፡ ተቋሙ ባስቀመጣቸው ባስቀመጣቸው መመዘኛዎች መሰረት ኢትዮጵያ እጅግ ከፍተኛ የግጭት ሁኔታ ውስጥ ልትገባ አንድ ደረጃ ብቻ ይቀራታል፡፡

አክሌድ በመላ ኢትዮጵያ ያሉ የፖለቲካ ግጭቶች እና የተቃውሞ ሰልፎች አዝማሚያ ላይ መረጃን ከየአከባቢው መሰብሰብ እና መተንተን ላይ የሚሰራ፣ ኢትዮጵያ ፒስ ኦብዘርቫቶሪ (ኢፒኦ) የተሰኘ ፕሮጀክት አቋቁሞ እየሰራ ነው፡፡

በአክሌድ ግምገማ መሰረት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶችን እያስተናገደች ትገኛለች። ሰፊ የሕዝብ አመጾች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ያመጡትን ከፍተኛ ለውጥ ተከትሎ፣ ኢትዮጵያን በአሁኑ ወቅት መንታ መንገድ ላይ የምትገኝ አገር መሆኗንም ጠቁሟል፡፡

ተቋሙ በብሔር ፌዴራሊዝም ላይ በተመሰረተው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ምህዳ ውስጥ ብሔርን መሰረት ባደረገው መዋቀር፣ ሥልጣን እና ግዛት ለማግኘት ኃይል የተቀላቀለበት የስልጣን ሽኩቻ ተፈጥሯል የሚል ግምገማ አለው።

@አንድ አፍታ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *