አጠቃላይ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት የደረሰ 33.6 % ሲሆን ምግብ ዋጋ በፌብራሪ ወር ስሌት በአንፃሩ ወደ 41.9 % ከፍ ብሎ ታይቷል።ይህም ማለት በምሳሌ ለማስረዳት ባለፈው ወር 100ብር ያወጣ የነበረ የፍጆታ እቃ አሁን 141.90 ያወጣል ማለት ነው።
Price Statistics
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በሙሼ ሰሙ
የወጭ ንግድ 12 % አድጓል፣ ገቢ ንግድ በ 8.1 % ቀንሷል በዚህም ምክንያት የከረንት አካውንት ጉድለት ከ5.3 ወደ 4.4 % ወርዷል። መንግስት ከቀረጥ የሚያገኘው ገቢ በ16% ያደገ ሲሆን ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (GDP) አኳያ ግን 0.8 ቀንሷል። 20/21 የስንዴ ምርት በ1.6 በመቶ በማደግ 5.18 ሚሊየን ቶን እንደሚደርስ ተገምቷል። በፈታኝ ሁኔታ ውስጥም ሆኖ ኢኮኖሚያችን 6% እድገት አሳይቷል። […]
የዚህ ወር የዋጋ ግሽበት 33 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል!
የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ መጥቷል የዚህ ወር የዋጋ ግሽበት በ33 ነጥብ 6 በመቶ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ። ምንም እንኳን አሃዙ በጥር ወር 2014 ከተመዘገበው 34.5 በመቶ በመጠኑ ያነሰ ቢሆንም፣ የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ መሄዱን ግልፅ ማሳያ ነው። ካለፈው አመት የካቲት ወር ጋር ሲነጻጸር የምግብ እቃዎች ዋጋ በአማካይ በ41.9 በመቶ ከፍ ብሏል። ጤፍ፣ ስንዴ እና በቆሎን ጨምሮ […]
የጥር ወር 2014 ዓ.ም የዋጋ ግሽበት ሁኔታ
የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ የዋጋ ግሽበት አጭር ማጠቃለያ፦ ባለፈው ወር 35.1 በመቶ ከደረሰ በኋላ፣ በጥር 2014 ዓመታዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 34.5 በመቶ በመጠኑ ዝቅ ብሏል። የጥር 2014 ወራዊ የምግብ ዋጋ ግሽበት ካለፈው ታህሳስ 2014 ጋር ሲነጻጸር በ1.7 በመቶ ቀንሷል። በተመሳሳይ ጊዜ ውስጥ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት 0.7 ከመቶ ጨምሮ ነበር። CSA



