Price Statistics

የዚህ ወር የዋጋ ግሽበት 33 ነጥብ 6 በመቶ ደርሷል!

የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ መጥቷል የዚህ ወር የዋጋ ግሽበት በ33 ነጥብ 6 በመቶ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ። ምንም እንኳን አሃዙ በጥር ወር 2014 ከተመዘገበው 34.5 በመቶ በመጠኑ ያነሰ ቢሆንም፣ የኑሮ ውድነቱ እየጨመረ መሄዱን ግልፅ ማሳያ ነው። ካለፈው አመት የካቲት ወር ጋር ሲነጻጸር የምግብ እቃዎች ዋጋ በአማካይ በ41.9 በመቶ ከፍ ብሏል። ጤፍ፣ ስንዴ እና በቆሎን ጨምሮ የእህል ምርቶች ከፍተኛ የዋጋ መጨመር ያሳዩ ሲሆን የአትክልቶች ዋጋ ግን በአንጻራዊ ሁኔታ መቀነሱን ዘገባው አመልክቷል። የምግብ ነክ ያልሆኑ ምርቶች የዋጋ ግሽበት 22.9 በመቶ ላይ ደርሷል።

ምንጭ፡- አዲስ ፎርቹን