Home National statistics

የመጭው 2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ አጠቃላይ በጀት 971.2 ቢሊየን ብር ሆኖ ለፓርላማው ቀረበ፡፡

ይህም ከ2016 በጀት ጋር ሲነፃፀር የ21.1 በመቶ እድገት እንዳለው ረቂቅ በጀቱን ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ ከዚህ የወጪ በጀት ውስጥ 451.3 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ በጀት፣ 283 .2 ቢሊየን ለካፒታል እንዲሁም 236.7 ቢሊየን ብር ለክልሎች የበጀት ድጋፍሆኖ መደልደሉን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ለክልሎች ከተመደበው በጀት ውስጥ 14 ቢሊየን ብር የሚሆነው የዘላቂ ልማቶችን ለማስፈፀም ለክልሎች የተመደበ ድጋፍ እንደሆነ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡ ከቀረበው የፌዴራል መንግስት የወጪ በጀት ውስጥ ከፍተኛውን በጀት፤ ለመደበኛው የተያዘው በጀት እንደሆነ የተናገሩት የገንዘብ ሚኒስትሩ ይህም የጠቅላላውን በጀት 46.5 በመቶ ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡

ሰኔ 30 ከሚጠናቀቀው ከ2016 በጀት ዓመት ጋርም ሲመሳከር የ21.9 በመቶ እድገት እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ከመደበኛ በጀት ውስጥ 128.2 ቢሊየን ብር ወይንም 28.2 በመቶ ለመደወዝ፣ ለአበል እና ለልዩ ልዩ ክፍያ ሲሆን 321.4 ቢሊየን ወይም 71.8 በመቶ ለስራ ማስኬጃ ተደግፎ የቀረበ መሆኑን አህመድ ሽዴ ተናግረዋል፡፡

Source: Natnaelfb

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *