በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል ማቸስተር ዩናትድን በሜዳው በማሸነፍ ወደ ፕሪምየር ሊጉ መሪነት ተመልሷል።
በዛሬው እለት በአርሰናል እና በማንቸስተር ዩናይትድ መካከል የተደረገው ጨዋታ በአርሰናል 1ለ0 አሸናፊነት የተጠናቀቀ ሲሆን፤ አርሰናል ወሳኝ ድል ማስምዝገብ ችሏል።
የአርሰናልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብም ትሮሳድ በ20ኛ ደቂቃ ላይ ከመረብ አሳርፏል።
ይህንን ተከትሎም አርሰናል በ86 ነጥብ የፕሪምየርሊጉን የመሪነት ስፍራ ሲረከብ፤ ቀሪ አንድ ጨዋታ ያለው ማንቸስተር ሲቲ በ85 ነጥብ 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ሊቨርፑል በ78 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። በዛሬው እለት በሜዳው በአርሰናል የተሸነፈው ማንቸስተር ዩናትድ በ54 ነጥብ 8ኛ ደረጃ ላይ ተቀመጧል።
source: አል ዐይን