የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት የሚታወቀው ቴስላ ኩባንያ አሽከርካሪ አልባ የታክሲ አገልግሎት እንደሚጀምር አስታውቋል።
የቴስላ ኩባንያ መስራች የሆነው ኢለን መስክ በኤክስ አካውንቱ እንደገለጸው የፊታችን ነሀሴ 8 ላይ ቴስላ የመጀመሪያውን ሮቦት ታክሲ አገልግሎት ይጀምራል ብለዋል።
እንደ ኢለን መስክ ገለጻ ሹፌር አልባ የታክሲ አገልግሎት በተለይም ድካም እና አልኮል የጠጡ ሰዎች ይህን አገልግሎት ይጠቀማሉ ብሏል።
ምንጭ:- አልአይን