በኢትዮጵያ 71 በመቶ የሚሆነው ዜጋ በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኝ ቢሆንም የሚፈጠረው የስራ እድል ግን ከ50 በመቶ በታች መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ወንድማገኝ ታዬ ለአራዳ ገልጸዋል።
በዚህም በየዓመቱ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጋ ዜጋ ስራ አጥ እንደሚሆን የሴንትራል ስታቲስቲክስ ዳታ ጥናት ያመላክታል ነው ያሉት ባለሙያው።
የህዝብ ቁጥር መጨመርና ከኢኮኖሚ እድገቱ ጋር አለመመጣጠን፣ ከማምረቻው ዘርፍ ይልቅ የአገልግሎት ዘርፉ መስፋፋትና የሚቀጥረው ሰው አነስተኛ መሆን የራሱ ድርሻ እንዳለውም ጠቅሰዋል።
በተጨማሪም ከሚፈጠር የስራ እድል ውስጥ 80 በመቶው በመንግስት በኩል መሆኑም ለዚህ የራሱ ድርሻ አለው ነው ያሉት።
ይህን ለመቅረፍም የግሉ ዘርፍ ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ በስፋት መስራት እንዳለባቸው ባለሙያው አስገንዝበዋል።
ከዚህ ባለፈም የመስራት ባህልን ማሳደግ፣ የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎትና መሰል የመፍትሄ መንገዶችን መጠቀም እንደሚገባም አስረድተዋል።
ምንጭ :አራዳ ኤፍኤም